የጨረታ ማስታወቅያ

0
1058

የጨረታ ማስታወቅያ

ገዳ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩ  የደረቅ ጭነት  ተሽከርካሪ   መለዋወጫዎች እና ሌሎች መለዋወጫዎችን  በግልጽ ጨረታ   አወዳድሮ መግዛት  ይፈልጋል፡፡  ስለሆነም በጨረታዉ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡

ተ.ቁ የሚገዙ  እቃዎች  ዝርዝር መለኪያ ብዛት
1 ሀንጋሪ ሽራ9*12M (አንደኛ ደረጃ) በቁጥር 100
2 Plastic canvas 9*12M በቁጥር 100
3 ሀንጋሪ ሽራ 9*22 M (አንደኛ ደረጃ) በቁጥር 100
4 Plastic canvas 9*22M በቁጥር 100
5 Steel cable *12mm (ካቦ 12ሚ.ሜ) ሜትር 18,000
6 Nilonrop*12mm (ገመድ12ሚ.ሜ) ሜትር 30,000
7 አጠና እንጨት (ለሸራ ማሰሪያ) 9 Metre የሚረዝም በቁጥር 17,000

 

  1. በዘርፉ የተሰማሩ ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና አሰፈላጊዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  2. ማንኛዉም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚዉል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ  ህንጻ 12ኛ ፎቅ   ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ 11፡00 በመምጣት  የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛዉም ተጫራች በገዛዉ የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና በመፈርም በሰም በታሸገ ፓስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሀምሳ ሺ) ብር በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸዉ ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ እና ቴክኒካል ሰነድ  ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዬ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸዉ
  5. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋዉን ዉል ማስከበሪያ 10 % በማስያዝ ዉል መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሸያ ማድረግ እና እራሳቸዉን ከጨረታ ማግለል አይቻልም
  7. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለዉም
  8. ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቅያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚዉል ሆኖ በ16ኛዉ ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛዉ እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት  የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ፤ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ

አድራሻ :- ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ  ህንጻ 12ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-558-25-19

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here