የጨረታ ማስታወቅያ

0
1445

ገዳ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ የጋራዥ እቃዎች እና የህዝብ ማመላለሸ ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለሆነም በጨረታዉ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማሩ ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና አስፈላጊዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  2. ማንኛዉም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚዉል ሲሆን መስቀል አደባባይ ፓን አፍሪካን ህንጻ 2ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 10 ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛዉም ተጫራች በገዛዉ የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና በመፈርም በሰም በታሸገ ፓስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 40,000 (አርባ ሺ) ብር በሲፒኦ ወይም በቼክ ማቅረብ ያለባቸዉ ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዬ ፖስታ በማሸግ ሶስቱንም በዋና ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸዉ
  5. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋዉን ዉል ማስከበሪያ 10 % በማስያዝ ዉል መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መመዝገብያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሸያ ማድረግ እና እራሳቸዉን ከጨረታ ማግለል አይቻልም
  7. በሌላ ተጫራች ላይ ተ
  8. ንተረሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም
  9. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለዉም
  10. ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ብር ከአሸናፊ ጋር ዉል እንደተፈጸመ በኋላ ተመላሽ ይሆናል፡፡
  11. ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቅያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚዉል ሆኖ በ16ኛዉ ቀን በ8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዛዉ እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የታወጀበት ቀን: 04/08/2013

አድራሻ: መስቀል አደባባይ ፓን አፍሪካ ህንጻ 2ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-558-19-55

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here