የጨረታ ማስታወቅያ

0
1671

ቀን 02/06/2013ዓ.ም

የጨረታ ማስታወቅያ

ገዳ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በገላን መጋዘን ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ጎማዎች እና የተሸርካሪ ባትሪዎች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ፡፡

 1. ማንኛዉም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ በማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ የሚዉል ሲሆን መስቀል አደባባይ ፓን አፍሪካን ህንጻ 2ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 10 ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ 11፡00 በመምጣት  የማይመለስ 50 (ሀምሳ) ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
 2. ማንኛዉም ተጫራች በገዛዉ የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና በመፈርም በሰም በታሸገ ፓስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 3,000(ሶስት ሺ) ብር በሲፒኦ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና  ማቅረብ አለባቸዉ
 4. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ያሸነፉትን እቃ ማንሳት አለባቸዉ ፡፡
 5. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መመዝገብያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሸያ ማድረግ እና እራሳቸዉን ከጨረታ ማግለል አይቻልም
 6. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተረሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም
 7. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለዉም
 8. ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ብር ከአሸናፊ ጋር ዉል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል፡፡
 9. ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቅያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ የሚዉል ሆኖ በ10ኛዉ ቀን በ8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዛዉ እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት  የሚከፈት ይሆናል፡፡
 10. የጨረታ መክፈቻ ቀናት በበዓላት እና እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል
 11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ

አድራሻ መስቀል አደባባይ ፓን አፍሪካ ህንጻ 2ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-558-19-55

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here