ገዳ ትራንስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የትራንስፖር ባለስልጣን ባወጣው መመሪያ መሰረት ለደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎች የተቀናጀ የተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ (ጂ.ፒ.ኤስ) መሳሪያ በዘረፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በማወዳደር ማስገጠም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረዉን መስፈርት የምታሟሉ እና የፈዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ባወጣዉ መመሪያ ቁጥር 27/2011 መስፈርት የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
- በኢትዬጽያ ደረጃዎች ኤጄንሲ በጸደቀዉ የዲቫይስ ስታንዳርድ መሰረት እና ከፌዴራል ትራንስፖርት ቢሮ እውቅና ያለው
- በዘርፉ የተሰማሩ ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና እፈላጊዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ማንኛዉም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚዉል ሲሆን መስቀል አደባባይ ፓን አፍሪካን ህንጻ 2ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 10 ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች በገዛዉ የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና በመፈርም በሰም በታሸገ ፓስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የተወዳደረበትን ዋጋ 2 % የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ማቅረብ ያለባቸዉ ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዬ ፖስታ በማሸግ ሶስቱንም በዋና ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸዉ
- የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋዉን ዉል ማስከበሪያ 10 % በማስያዝ ዉል መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መመዝገብያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሸያ ማድረግ እና እራሳቸዉን ከጨረታ ማግለል አይቻልም
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተረሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለዉም
- ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ብር ከአሸናፊ ጋር ዉል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል፡፡
- ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቅያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚዉል ሆኖ በ16ኛዉ ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛዉ እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀናት በበዓላት እና እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ
አድራሻ መስቀል አደባባይ ፓን አፍሪካ ህንጻ 2ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-558-19-55